category stringclasses 4
values | headline stringlengths 17 80 | text stringlengths 1 16.8k | url stringlengths 36 49 |
|---|---|---|---|
sports | የስፖርት ኮከቦች እና የንግድ ምልክቶቻቸው- ከቦልት እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ | የአትሌቲክሱ ዓለም ኮከብ እና ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ከውድድር በፊት እና በኋላ የሚያሳየውን ታዋቂ የሆነውን ምልክት ለንግድ ምልክትነት ለመጠቀም ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል። እሱ ብቻ ግን አይደለም የሚለይበትን ምልክት የሚያሳይ ኮከብ። የአሜሪካ የፓተንት እና የንግድ ምልክት ቢሮ እንደገለጸው ቦልት ታዋቂውን ምልክቱን በንግድ ምልክትነት ለማስመዝገብ ማመልከቻውን ነሐሴ 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ አስገብቷል። መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ያደረጉት የንግድ ምልክት ጠበቃው ጆሽ ገርበን “አንድ እጁ ታጥፎ ወደ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/ceknk30j2xxo |
sports | እግር ኳስ፡ ዩናይትድ፣ አርሴናል፣ ቼልሲ . . . ምን አስበዋል? | የስፖርት ጋዜጦች ስለ እግር ኳስ ምን እያሉ ነው? በሚቀጥለው ጥር የሚከፈተው የዝውውር መስኮትስ ምን ያሳየን ይሆን?ዋና ዋናዎቹን በዚሀች አጭር ዘገባ እንዳስሳለን። አላንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ኧርሊንግ ብራውት አላንድ ፈላጊው በዝቷል። አሁን ደግሞ ቼልሲዎች ተጫዋቹን ለማስፈረም ዕቅድ እንዳላቸው እየተነገረ ነው። ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲዎች ተጫዋቹ የእኛ ነው እያሉ ነው። ይህን የዘገበው '90 ሚኒት' ጋዜጣ ነው። ቼልሲ አላንድንና የዌስትሃሙን ዴክሌን ራይስ ለማስፈረም ሰባት ተጫዋቾቹን ሊሸጥ እ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55435608 |
business | ዓለምን ካስጨነቃት የዋጋ ንረት ተጠቃሚዎቹ እነማን ናቸው? | ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጽእኖ ሳያገግም የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት የገጠመው የዓለም ምጣኔ ሃብት ከቀውስ አዙሪት ውስጥ አልወጣም። የነዳጅ እና የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት በመላው ዓለም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል። ታዲያ ዓለም በዋጋ ንረት በምትጨነቅበት በአሁኑ ወቅት በተለየ ሁኔታ ትርፍ እያጋበሱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዘርፎች አሉ። እነዚህ ከዋጋ ንረት የሚያተርፉ ድርጅቶች የትኞቹ ናቸው? | https://www.bbc.com/amharic/articles/crgj31l8mzzo |
health | ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በምርጫ አሸነፉ | በኮሮናቫይረስ የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በቅርቡ የተደረገውን ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፈዋል። 64 በመቶ የመራጮችንም ድምፅ ማግኘት ችለዋል። በደቡባዊቷ ሮማኒያ በምትገኘው ግዛት ዴቬሴሉ ከንቲባ የነበሩት ኢዮን አሊማን ለሶስተኛ ጊዜም አሸንፈዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት በመዲናዋ ቡካሬስት ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ከንቲባ ስም ከተመራጮች ዝርዝር ውስጥ ነበር። የተመራጮች ዝርዝር ቀድሞ በመታተሙ ስማቸውን ማስወገድ እንዳልተቻለም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የሞተ ሰው ከንቲባ ሆኖ እንደ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54336166 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት? | የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው። በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘ... | https://www.bbc.com/amharic/53627279 |
politics | ቤኒቶ ሙሶሊኒ ላይ የተኮሰችው አየርላንዳዊት | ጊዜው በፈረንጆቹ ሚያዝያ 7 1926 ነበር። ቦታው ደግሞ የጣልያኗ መዲና ሮም። የሃገሬው ሰው በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ ኃያላን መካከል አንዱ የነበረውን ግለሰብ ለማየት ተኮልኩሏል። አንዲት አየርላንዳዊት ሴት ግን በሰውዬው ወሬ ብዙም አልተማረከችም። ዓላማዋ ሌላ ነበር። ድንገት የተኩስ ድምፅ ተሰማ። ሰው ወዲያ ወዲህ ተበታተነ። ለተሰበሰበው ሰው መልዕክቱን ሲያስተላልፍ የነበረው ቤኒቶ ሙሴሊኒም ወደኋላ ተዘረጋ። ጥይቷ የፈለቀችው ከአየርላንዳዊቷ ሴት አፈሙዝ ነበር። ዒላማዋን አልሳተችም። የሙሶሊኒን አፍ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56145284 |
business | ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? | ኮሮናቫይረስ የማይነካው ነገር እንደሌለ እየታየ ነው። በየሰበብ አስባቡ እያሻቀበ የነበረውን ነዳጅ ዘይትን ሊነካው ዳርዳር እያለ ነው። በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ትልልቆቹ የነዳጅ አምራች አገራት በሽታው ካስከተለው ችግር ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ምርታቸው ሊቀንስ ይችላል እየተባለ ነው። የነዳጅ ዋጋን ለመደገፍ እርምጃ እንዲወሰድ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አምራች አገራት ማህበር የሆነው ኦፔክ እና አጋሮቹ በዚህ ሳምንት ስብሰባ እንደሚቀመጡ እየተጠ... | https://www.bbc.com/amharic/news-51368390 |
sports | በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የቤልግሬዱ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና | ሰርቢያ ቤልግሬድ ውስጥ ዛሬ ከመጋቢት 9 ተጀምሮ አስከ 11/2014 ዓ.ም በሚቆየው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አፍሪካዊያን አትሌቶች ሜዳሊያ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኬንያዊው አትሌት ፈርዲናንድ ኦሙርዋ ኦማንያላ ከእነዚህ መካከል አንዱ ሲሆን የዩሴይን ቦልትን የ100 ሜትር የዓለም ክብረወሰን መስበር እንደሚችል ተናግሯል። ኬንያዊው አትሌት በሰርቢያው ሻምፒዮና ውድድሩን 60 ሜትር ይጀምራል። የ26 ዓመቱ አትሌት በ9.77 በሆነ ሰከንድ የአፍሪካን የ100 ሜትር ክብረወሰን በእጁ አስገብቷል።... | https://www.bbc.com/amharic/news-60788088 |
politics | ምርጫ 2013፡ የምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይገለጻል ተባለ | ሰኞ ዕለት የተካሄደው ምርጫ ውጤት በምርጫ ክልል ደረጃ ረቡዕና ሐሙስ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው ምርጫ ጣቢዎች ውጤቶች ከማክሰኞ ንጋት ጀምሮ ይፋ ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን፤ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ወደ ምርጫ ክልሎች ከተላኩ በኋላ "ነገ [ረቡእ] እና ከነገ ወዲያ [ሐሙስ] የምርጫ ክልል ውጤት ይፋ ይደረጋል" ሲሉ የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል። የምርጫ ክልል ውጤቶች ደግሞ ከመላው አገሪቱ ወደ ማዕከል ገብተው አስፈላጊው ማጣራት ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57554222 |
health | በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው | በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው ... | https://www.bbc.com/amharic/54744271 |
business | "የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል" | በመጪዎቹ ዓመታት በአሜሪካና በቻይና መካከል ሊከሰት የሚችለው ቀዝቃዛ ጦርነት ዓለምን ከኮሮናቫይረስ በላይ ሊያስጨንቅ እንደሚገባ ዕውቁ የምጣኔ ሀብት ሊቅ ጄፍሪ ሳክስ ተናገሩ። የኮሎምቢያው ዩኒቨርስቲ ዕውቅ ፕሮፌሰር ጄፍ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዓለም ወደ አንዳች መደነቃቀፍ እያመራች ነው፤ መሪ አልባም ሆናለች ብለዋል። እንዲሁም የዓለም ሁኔታ መልክ ባልያዘበት ሁኔታ በሁለቱ የዓለም ኃያላን መካከል ያለው ቁርሾና ቅራኔ እየባሰ ከሄደ ሁኔታዎችን ያባብሳል፤ ጦሱም ለተቀረው ዓለም ይተርፋል ብለዋል። እኚህ ፕሮፌ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53135326 |
health | በኮሮና የተያዙ ሰዎች በድባቴ እና የመርሳት በሽታ የመጠቃት እድላቸው እንደሚጨምር ጥናት አመለከተ | ባለፈው ስድስት ወራት ውስጥ የኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች በድባቴ፣ የመርሳት በሽታ፣ ስትሮክ እና በሳይኮሲስ ህመሞች የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን በኦክስፎርድ ተመራማሪዎች የተሰራ ጥናት አመላከተ። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ቀድመው የነበሩባቸው የስነ ልቦና እና የነርቭ ችግሮች ያገረሽባቸዋል ወይም እንደ አዲስ ሕመሞቹ ያጠቋቸዋል ሲል ጥናቱ አመልክቷል። በቫይረሱ ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ወይም በፅኑ ህሙማን ማቆያ ከነበሩ ደግሞ የመያዝ እድላቸው የበለጠ ይሰፋል ሲል ጥናቱ አመላክቷል። እነዚህ ጫና... | https://www.bbc.com/amharic/news-56664358 |
sports | ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሁሉ ቀድመው ካሜሮን የገቡት ዋሊያዎች | በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሁንም በወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ሆኖ በመጪው ወር ጥር 01/2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ መካሄድ ይጀምራል። በዚሁ ውድድር መሳተፋቸውን ያረጋገጡት ዋልያዎቹም ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ቀድመው ካሜሩን በመድረስ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ጌታነህ ከበደን ጨምሮ 25 ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፣ ካፍ ካስቀመጠው ገደብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌ... | https://www.bbc.com/amharic/news-59840259 |
health | የተከተቡ ሰዎች ለምን በድጋሚ ኮሮናቫይረስ ይይዛቸዋል? | ኮቪድ የሰው ልጅን የሙጥኝ እንዳለ አለ። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል እና ሌሎም አገራት ውስጥ ኦሚክሮን ተመልሶ እያመሳቸው ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሆስፒታል አልጋን እየያዙ ነው። ከእነዚህ የሚበዙት የተከተቡ ናቸው። ታዲያ መከተብ ከተህዋሲው ካልተከላከለ ምንድነው ፋይዳው? እርግጥ ነው ተከተቡ በተባሉ ሰዎች የሚታይ የጎንዮሽ ጉዳት ዝቅተኛ ነው። ብዙ ሰዎች በድኅረ ክትባት ጊዜ ከትኩሳት፣ ከራስ ምታት፣ ከክንድ መለስተኛ ሕመም፣ ከድካምና ከማቅለሽለሽ የከፋ ስሜት አይሰ... | https://www.bbc.com/amharic/news-59925005 |
politics | ኡጋንዳ ከሙዚቀኛው ተቃዋሚ ጋር ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠየቀች | የኡጋንዳ መንግሥት ከታዋቂው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠይቋል። በኡጋንዳ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን በዋነኝነት የሚቆጣጠረው አካል አስራ አራት የዩቲየብ ቻናሎች እንዲዘጉ ጠይቋል። ተቆጣጣሪው አካል ደብዳቤውን የፃፈው የዩቲዩብ ባለቤት ለሆነው ጉግል ሲሆን በባለፈው ወር ከደረስው ነውጥም ጋር ግንኙነት ያላቸውና ለ50 ሰዎችም መሞት ተጠያቂ ናቸው ያላቸው እንደሆነም አስፍሯል። በአገሪቱ ውስጥ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ሮበርት ካያጉላንይ ወይም ቦቢ ዋይን እስር ተከትሎ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55329580 |
sports | እግር ኳስ፡ አምስት ቁልፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ | ኢትዮጵያ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ከኒጀር ጋር ለምታደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ተጠርተው ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል አምስት ቁልፍ ተጫዋቾች ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው ተነገረ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ለብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተው ከነበሩት 36 ተጫዋቾች መካከል ለቡድኑ ወሳኝ የሆኑት አምስት ተጫዋቾች በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አቶ ባህሩ ለውድድሩ 41 ተጫዋቾች መጠራታቸውን አስታውሰ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54417243 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጂን እጥረት በርካቶች በሚሞቱባት ሕንድ ሆስፒታል ላይ በተነሳ እሳት 13 ህሙማን ሞቱ | ዛሬ አርብ በሕንዷ ከተማ ሙምባይ አቅራቢያ ባለ ኮቪድ-19 ህክምና ሆስፒታል ላይ በተነሳ ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። አርብ ጠዋት የተቀሰቀሰው እሳት ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆነ በኋላ በቁጥጥር ሰር የዋለ ሲሆን ከአደጋው ተረፉት ህሙማን በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተዘዋውረዋል። በርካታ ሰዎች በወረርሽኙ እየተያዙባት ባለችው ሕንድ በዛሬው ዕለት ብቻ 332,730 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በዓለም በአንድ ቀን የተመዘገበው የህሙማን ቁጥር ነው ተብሏል። በበሽታው ሰበብ ህይወታ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56827449 |
sports | የጀርመን ቡንደስሊጋ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' ያላቸውን ድጋፍ አሳዩ | የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ ተቃውሞዎች አሳይተዋል። የብሮሲያ ዶርትሙንድና ሄርታ በርሊን ተጫዋቾች በሲግናል ኢዱና ፓርክ በመገኘት ሜዳውን በመክበብም በጉልበታቸው ተንበርክከው ነበር። የዶርትሙንድ ተጫዋቾች ከውድድሩ በፊት ሲያሟሙቁ "ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም" እንዲሁም "ተባብረን እንቁም" የሚሉ መልእክቶች በተፃፈባቸው ማሊያዎች (ካናቴራዎች) ነው። የባየር ሙኒክ ተወዳዳሪዎች "ለዘረኝነት ቀይ ካርድ" የሚል ማሊያ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-52954511 |
health | የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል | በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። "በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ... | https://www.bbc.com/amharic/54708506 |
health | የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ | በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች... | https://www.bbc.com/amharic/news-56827450 |
business | መንግሥት በኦሮሚያ ባለው ታጣቂ ቡድን ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ | የመንግሥት ኃይል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሰጡት መግለጫ፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውንና መንግሥት 'ሸኔ' ሲል በአሸባሪነት የፈረጀውን ታጣቂ ኃይል ለማስወገድ ፀረ ሽምቅ ውጊያ ኮማንዶ በማሰማራት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ዘመቻው በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ እና በምሥራቅ... | https://www.bbc.com/amharic/news-61435712 |
business | ‘ፓትሪዮት’፡ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጣት ብዙ የተነገረለት አየር መቃወሚያ | ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ምዕራባዊያንን አጥብቀው ሲጠይቁ የነበረው አንድ ነገር የአየር መቃወሚያ እንዲሰጣቸው ነበር። ምክንያቱም ሩሲያ በአየር ኃይሏ ኪዬቭን ጨምሮ ዋና ዋና ከተሞችን በጨለማ እንዲዋጡ አድርጋለች። በካሚካዚ ድሮንና በተወንጫፊ ሚሳኤሎች ብዙ ጥፋት አድርሳለች። ውሃና መብራት ለሚሊዮኖች ቅንጦት ሆኖ እንዲሰማቸው ሆኗል። ዩክሬናውያን የውርጩን ዘመን ያለማሞቅያ በብርድ እየተንዘፈዘፉ እንዲኖሩ ተደርገዋል። በዩክሬን ብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ ነው የሚከፋፈለው። ከዚህም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በዩክ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g43d1n4dko |
politics | ሩሲያ እና ዩክሬን: ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዴት ፈጠረች? | ሩሲያ በቅርብ አመታት በአፍሪካ ተጽዕኖዋን እያሰፋች ነው። ከዩክሬን ወረራ በኋላ አዳዲሶቹ አጋሮቿ ድጋፍ እንዲሰጧት ወይም እንደተባበሩት መንግሥታት ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢያንስ ገለልተኛ ሆነው እንዲቆዩ ትጠብቃለች። ከሊቢያ እስከ ማሊ፣ ሱዳን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በሞዛምቢክ እና ሌሎችም ሃገራት ሩሲያ ይበልጥ እየተሳተፈች ነው። አብዛኛው ተሳትፎዋ ደግሞ በወታደራዊ ኃይል ሲሆን አማፂያንን ወይም የጂሃዲስት ታጣቂዎችን መዋጋትን ይጨምራል። ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60543495 |
politics | የፑቲንን አስተዳደር ሙስና የሚታገሉት የሩስያ ሴቶች | ወንዶች ጎልተው የወጡበትን የሩስያ ፖለቲካ ለመለወጥ ሙስናን የሚቃወሙ ሴቶች ቆርጠው ተነስተዋል። እነዚህ ሴቶች የለውጥ ተምሳሌት ተብለዋል። ከተቃዋሚው አሌክሲ ናቫልኒ ጋር ይሠራሉ። ናቫልኒ የጸረ ሙስና ንቅናቄን ማዕከል ያደረገው ኤፍቢኬ ፓርቲውን ለፓርላማ ምርጫ ሲያዘጋጅ የእነዚህ ሴቶች ሚና ጉልህ ነው። የሩስያ ፓርላማ ለፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታማኝ ነው። አብላጫውን ቁጥር የያዙትም ወንዶች ናቸው። ከታህታይ ምክር ቤቱ የሴቶች ድርሻ 16% ሲሆን ከላዕላይ ምክር ቤቱ ደግሞ 17% መቀመጫ አላቸው። በናቫ... | https://www.bbc.com/amharic/56066793 |
health | ለ15 ወራት ደሞዛቸው ያልተከፈላቸው የትግራይ የሕክምና ባለሙያዎች | የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ኃይሎች ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ማጀታቸው የሞላ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የሚልኩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የሚተርፉ ነበሩ። በመቀለ የሚገኙ እና ቢቢሲ ያነጋገራቸው መምህራን፣ የሕክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት የነበራቸው ሕይወት የዛሬውን አይመስልም ነበር። ዛሬ በትግራይ ያለው ጦርነት ተባብሶ፣ በክልሉ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሥራ አቁመው፣ የሰብዓዊ እርዳታ ተመናምኖ ሁሉም የሰው እጅ ጠባቂ እንደሆ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgegl7dd8k7o |
sports | እግር ኳስ ፡ የዲያጎ ማራዶና የአስከሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ | ከአንድ ወር በፊት በልብ ችግር ምክንያት ያረፈው የቀድሞው የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አስከሬን ላይ የተደረገው ምርምራ ይፋ ሆነ። የአርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ የአስከሬን ምርመራ እንዳረጋገጠው ህይወቱ ባለፈበት ጊዜ ምንም አይነት አልኮልም ሆነ ዕጽ መውሰዱን የሚያሳይ ምልክቶች እንዳልተገኙ ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ 1986 ላይ በተደረገው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ ኮከብ በመሆን አገሩ አርጀንቲና በአሸናፊነት ዋንጫ እንድትነሳ ያስቻለው ማራዶና በኅዳር ወር ላይ ነበ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55458658 |
health | በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? | ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54009884 |
business | 'ገበሬው አምርቶ የማይጠቀምባት ኢትዮጵያ' የኑሮ ውድነቱን እንዴት መቀነስ ትችላለች? | በምጣኔ ሃብታዊ ቋንቋ የአቅርቦት ሰንሰለት ይባላል። በእንግሊዝኛው 'ሰፕላይ ቼይን' የሚባለው ማለት ነው። የአቅርቦት ሰንሰለት ሸማቹ ወይም ተገልጋዩ የሚፈልገው ነገር ለገበያ እስኪቀርብ ድረስ ያለው ሂደት ነው። የምጣኔ ሃብት ሰዎች የአቅርቦት ሰንሰለት የአንዲት ሃገር ዕድገት ምሰሶ ወይም ከምሰሶዎች አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ይላሉ። የአቅርቦት ሰንሰለትን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት ወደ አርባምንጭ እንሂድ። አርባምንጭ የፍራፍሬ ሃገር ናት። በተለይ ደግሞ ሙዝ። አንድ ፍሬ ሙዝ አርባምንጭ ላይ ያለው ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56920410 |
politics | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነውን ቶም ጋርድነር ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ። ዘጋቢው "የሙያ ስነ ምግባርና የሃገሪቱን ህግና መመሪያ መጣሱንም" በመግለፅ ባለስልጣኑ ለፈቃዱ መሰረዝ ምክንያት እንደሆነ በዛሬው ዕለት ግንቦት 5፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ባለስልጣኑ ጥሰቶች ብሎ ያሰፈራቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አልገለጸም። ባለስልጣኑ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት ከዚህ ቀደም ከዘጋቢው ቶም ጋርድነር ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች አድርገናል ብሏል።... | https://www.bbc.com/amharic/news-61441551 |
politics | በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማት ባልደረቦች የነበሩትን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸውን የደኅንነት ምክር ቤት አስታወቀ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማትን “የከዱ” የተባሉ አባሎችን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገለጸ። ምክር ቤቱ ትላንት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ “ከፀጥታ ተቋማት የከዱ አባላትን የመያዝ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር የማዋል” ሥራ መከናወኑ ተገልጿል። በአማራ ክልል ባለፉት ሳምንታት መንግሥት “የሕግ ማስከበር” በሚል በወሰደው እርምጃ፣ “ተበትነው የፀጥ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cx87elvg9j7o |
sports | እግር ኳስ ፡ የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ማልያ በልካቸው አለመሰፋቱ ቁጣን ቀሰቀሰ | የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን እያሰሙ ነው። የብሔራዊ ቡድኗ ከሜዳ ውጭ የምትጫወትበት ማልያ በአዲስ መልክ ቢሰራም ለሴቶች የሚሆን የለም ተብለዋል ደጋፊዎች። መቶ በመቶ ከፖሊስተር ጨርቅ የተሠራው አዲሱ ማልያ ባለፈው አርብ ከወንዶቹ ማልያ ጋር ነበር ለገበያ የቀረበው። ነገር ግን የሴቶች ብሔራዊ ቡድኗ በትዊትር ገጿ እንዳስታወቀችው አዲሱ ማልያ በሴቶች ልክ አልተሰራም፤ በወንዶች እንጂ በማለት ያጋጠመውን ችግር ገልጸዋል። 'ማቲልዳስ' ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54216906 |
health | የወባ በሽታን 70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመለከተ | በአንድ ጥናት መሰረት አዲስ አይነት የመከላከል መንገዶችን በመጠቀም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት በወባ በሽታ የመያዝና የመሞት ዕድላቸውን በ70 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተጠቆመ። የወባ በሽታ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸው ወራት ከመድረሳቸው በፊት ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግና በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች መከላከያ መድኃኒቶችን እንዲጨምሩበት በማድረግ ሙከራው ከፍተኛ የሆነ ውጤት ማስገኘቱን በለንደን የሚገኙ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። የዚህ የወባ በሽታን የመከላከል ሙከራው የተደረገው ከቡርኪናፋሶ እና ከማሊ የተወጣ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58345206 |
business | ቢሊየን ዓመት ያስቆጠረው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ | የዓለማችን ትልቁ የተቆረጠ አልማዝ ነው ተብሎ የሚታመነውና የቢሊየን ዓመት ዕድሜ ያለው ጥቁር አልማዝ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ። ዘ ኢኒግማ ተብሎ የተሰየመው የ555.55 ካራት አልማዝ ከአንድ ሙዝ ክብደት ጋር ተነጻጽሯል። በበይነ መረብ ግብይትም ከ4.4 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከአስትሮይድ ጋር ወደ ምድር መምጣቱን ጨምሮ ስለ አልማዙ አመጣጥ ብዙ መላ ምቶች አሉ። አጫራቹ ሶዝባይ እንዳለው፤ ገዢው ክፍያውን በክሪፕቶከረንሲ ለማድረግ መርጧል። ሶዝባይ የገዢውን ማንነት ሳይገልጽ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60329211 |
politics | ሩሲያ ለዩክሬን ተገንጣይ ክልሎች ዕውቅና ሰጠች | የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሲካሄድ የቆየው የሰላም ድርድር ማብቃቱን በመግለጽ በዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል ተገንጥለው ለሚገኙ አማፂ ክልሎችን ዕውቅና ሰጡ። ለራሳቸው ነጻነታቸውን ያወጁት የዶኔስክ እና የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊኮች በሩሲያ የሚደገፉ አማፂያን ሲሆኑ እአአ ከ2014 ጀምሮ ከዩክሬይን ጦር ጋር ሲዋጉ ነበር። የሩሲያ ወታደሮች በሁለቱም ክልሎች "የሰላም ማስከበር ሚናቸውን" እንዲወጡ ታዘዋል። ሩሲያ ሆን ብላ ሉዓላዊነታችንን እየጣሰች ነው ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሰዋል። ፕሬዚደንት ቮሎ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60474353 |
business | የመንደር ውል ሕጋዊ ነው? በመንደር ውል ቤት ስንሻሻጥ ልብ ልንላቸው የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች | የአገሪቱ አዋዋይ በተለምዶ 'ውልና ማስረጃ' የምንለው መሥሪያ ቤት ነው። የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ደግሞ ሙሉ ስሙ ነው። አሁን ግን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። ነገሩ ከወቅቱ የአገሪቱ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም። ከሐምሌ ወዲህ ይኸው እስከዛሬም አገልግሎት እየሰጠ ያለው በከፊል ነው። የተንቀሳቃሽ ንብረት ሽያጭን ጨርሶውኑ እያዋዋለ አይደለም። ይህን ተከትሎ ዜጎች በስፋት በመንደር ውል ተጠምደዋል። "ላልከዳህ-ላልክድህ ቃል አለኝ" እያሉ በየመንደሩ እየተፈጣጠሙ ነው... | https://www.bbc.com/amharic/59633486 |
health | ስትወለድ በክብደት የዓለማችን ትንሿ ጨቅላ የነበረችው ከዓመት በኋላ ከሆስፒታል ወጣች | ስትወለድ ከአንድ ብርቱካን ያነሰ ክብደት ትመዝን የነበረችው የዓለማችን ጨቅላ ከ13 ወራት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቤቷ ገባች። እምቦቅቅላዋ በሲንጋፖር ሆስፒታል ባለፉት 13 ወራት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ክትትል ሲደረግላት ቆይቷል። ዌክ ዩ ዥዋን ትባላለች። ስትወለድ የምትመዝነው 212 ግራም ነበር። ይህ ክብደት ማለት በአማካይ የአንድ ትንሽ ብርቱካን ክብደት ማለት ነው። ቁመቷ 24 ደግሞ ሴትቲ ሜትር ብቻ ነበር። አንድ ጤናማ ልጅ የሚወለደው በአማካይ ከ40 ሳምንታት ቆይታ በኋላ መሆኑ ይታወቃል። ይህቺ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58142407 |
sports | ኮሮናቫይረስ፡ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ ይችላሉ | የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሊጉ በቅርቡ ጀምሮ በዝግ ስታዲየም ቢጫወቱም እንኳን ለአገር ውስጥና ለዓለማቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ቢቢሲ ስፖርት ባገኘው መረጃ መሰረት ሊጉ ከነጭራሹ የሚቋረጥ ከሆነ አልያም ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች የሚኖሩ ካልሆነ ክለቦቹ ከተገለጸው ገንዘብ ተጨማሪ ሊከፍሉም ይችላሉ። • የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን? • ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል? የፕሪምረየር ሊግ ክ... | https://www.bbc.com/amharic/news-52629957 |
business | በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ | በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የትምህርት ክፍያ ጭማሪ በሚፈፅሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በርካታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተረድቻለሁ ብሏል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለስልጣን ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58391132 |
health | ኮሮናቫይረስ ፡ ስንት ተስፋ ሰጪ የኮቪድ-19 ክትባቶች ተገኝተዋል? | የተለያዩ ተቋሞች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት መቃረባቸውን እያስታወቁ ነው። ይህም ለመላው ዓለም ተስፋ የሰጠ ዜና ሆኗል። ከሳምንት በፊት ፋይዘር እና ባዮቴክ የተባሉ ተቋሞች ውጤታማነቱ አስተማማኝ የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሞዴርና የተባለ ድርጅት ውጤታማ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። በኦክስፎርድ የሚካሄደው የክትባት ምርምር በ60ዎቹ እና 70ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከማዳበር አንጻር ውጤታማ መሆኑ ተገ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55003274 |
sports | ሊቨርፑል ከ ማድሪድ፡ ታላቁ የአውሮፓ እግር ኳስ ፍልሚያ | ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የፈረንሳይዋ ዋና ከተማ ፓሪስ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የኃያላኑን ሪያል ማድሪድና ሊቨርፑል ፍልሚያ ታስተናግዳለች። ሁለቱ ቡድኖች ከአራት ዓመታት በፊት በዚሁ መድረክ ለፍጻሜ ተገናኝተው ማድሪዶች ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። እግር ኳስ የሚወድ ማንኛውም ሰው ይህ ጨዋታ እንዲያመልጠው አይፈልግም። እግር ኳስ ለምኔ የሚሉት እንኳን ስለነዚህ ቡድኖች ፍልሚያ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሰምተዋል። በአውሮፓ ቻምፒየንስ ታሪክ ዋንጫውን 13 ጊዜ በማንሳት ተወዳዳሪ የሌላቸው ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c10g9zzgd11o |
politics | ዶናልድ ትራምፕ በአምሳያቸው የተሠሩ የኤንኤፍቲ ስብስቦችን ለገበያ አቀረቡ | የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእሳቸው ፊት አምሳያ የተሰሩ የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሥራዎችን ይፋ በማድረግ ለገበያ አቀረቡ። ትራምፕ እነዚህ ውስን የሆኑት ዲጂታል ካርዶች የሥራ እና የጥበብ ሕይወቴን የሚያንጸባርቁ ናቸው ብለዋል። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ይፋ የማደርገው ጉዳይ አለ ማለታቸውን ተከትሎ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳግም ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ምክትላው አድርገው የሚያቀርቡትን ዕጩ ይፋ ሊያደርጉ ነው ተብሎ በስፋት ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cpeq0e92qveo |
health | ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው- የዓለም ጤና ድርጅት | አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ነገር ግን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ እንዳሉት ምናልባት እስካሁን ያልታወቁ በሌሎች አገራት ውስጥ ሊኖር ይችላል ብለዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ ልውጡን ዝርያ ለመጋፈጥ በቂ ስራ አለመሰራቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። "በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ ቫይረስ የጋረ... | https://www.bbc.com/amharic/news-59662932 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ የስፔን ቀብር አስፈጻሚዎች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ | በስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች በኮሮረናቫይረስ የሚሞሩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የሰራተኛ ቁጥር ይጨመርልን በማለት የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል። የሰራተኞች ማህበራት እንደገለጹት ወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ሲከሰት ቀብር አስፈጻሚዎቹ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የአንዳንድ ሰዎችን ቀብር ሳይፈልጉ እንዲያራዝሙ ተገድደዋል። በአሁኑ ሰአት ደግሞ አውሮፓ በሁለተኛ ዙር የቫይረሱ ስርጭት እየተፈተነች ትገኛለች። በርካታ አገራት ቫይረሱ እንደ አዲስ መሰራጨት መጀመሩን ተ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54776071 |
politics | የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የኡጋንዳው የትራንስፖርት ሚንስትር ቆሰሉ | የኡጋንዳ የትራንስፖርት ሚንስትር በታጣቂዎች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የቆሰሉ ሲሆን የሚንስትሩ ልጅና ሹፌር ግን በጥቃቱ መገደላቸው ተገለጸ። የቀድሞው የመከላከያ ኃላፊና የአሁኑ የትራንስፖርት ሚንስትር ጄነራል ካቱምባ ዋማላ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ካምፓላ የሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። በሞተርሳይክል ይጓዙ የነበሩ ታጣቂዎች የሚንስትሩ መኪና ላይ ደጋግመው መተኮሳቸው ነው የተነገረው። ከግድያ ሙከራው ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ የስልክ ጥሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄ እን... | https://www.bbc.com/amharic/57318950 |
politics | በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ የጂቡቲ ወታደሮችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ | በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት የጂቡቲ ወታደሮችን አስለቅቆ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወታደሮቹ ፍሩድ (ዘ ፍሮንት ፎር ዘ ሪስቶሬሽን ኦፍ ዩኒቲ ኤንድ ዲሞክራሲ) በተሰኙ የጂቡቲ ታጣቂዎች ታግተው እንደነበርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮቹን ከታጣቂዎቹ እገታ ማስለቀቅ የቻለው በተቀናጀ ስለላ እና የፖሊስ ዘመቻ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cyek0y9zw80o |
sports | እስራኤል ፡ አረቡ ባለሃብት በእስራኤሉ ዘረኛ ክለብ ላይ ገንዘባቸውን ለማፍሰስ ለምን መረጡ? | ከቀናት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፅንፈኛ የሚባለው የእስራኤሉ ቤይታር ጄሩሳሌም እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን ልምምድ በማቋረጥ ሜዳውን ወረሩት። ደጋፊዎቹ በቁጣና በንዴት ሜዳውን የወረሩት ክለቡ ከሚወዳደርበት የእስራኤል ሊግ ወደታች ለመውረድ እየተንገታገተ በመሆኑ አይደለም። ነገሩ ወዲህ ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆኑት ቱጃር በክለቡ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው ቁጣቸውን የገለፁት። ክለቡም ከሁለት ቀናት በፊት ከሼክ ሃማድ ቢን... | https://www.bbc.com/amharic/news-55241937 |
business | ሕንድ ውስጥ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያውጣ ኮኬይን ተያዘ | የሕንድ ባለሥልጣናት ጉጃራት በምትባለው ግዛት ወደ 3ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለውን አደንዛዥ ዕጽ መያዛቸውን አስታወቁ። ይህ በጉጃራት በሚገኝ ወደብ ላይ የተያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ ኮኬይን ለገበያ ቢቀርብ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያወጣል ተብሏል። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና በርካታ ሰዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል። የኮኬይኑ መነሻ አፍጋኒስታን መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በይፋዊ ሰነዶች ላይ እቃው 'ታልክ' የተሰኘ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58640077 |
sports | በአከራካሪው የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች | ኳታር ዶሃ ላይ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ በወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸነፈ። ይህ በሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር በለሜቻ ግርማ የተገኘው የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በዘርፉ የመጀመሪያ ሲሆን የተመዘገበው ሰዓትም ለአገሪቱ ክብረ ወሰን ነው ተብሏል። ኬንያዊው አትሌት የወርቅ ሜዳሊያውን በወሰደበት በዚህ የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ለሜቻ የተቀደመው ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጠባ... | https://www.bbc.com/amharic/49944141 |
sports | የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር ምርጫ ያስከተለው ውዝግብ | ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ጋር በተያያዘ ውዝግብ መከሰቱ ሲነገር ቆይቶ ሰኞ ዕለት በኮሚቴው ጽህፈት ቤት ውስጥ ተካሄደ የተባለን ስብሰባ ተከትሎ በአካባቢው ተቃውሞ እንደነበር ተሰምቷል። ይህ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ደጃፍ የተደረገው የተቃውሞ ሠልፍ የተጠራው የኮሚቴው አባል በሆነው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደነበረ የፌዴሬሽኑ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቃውሞ ሠልፉን ያደረጉበትን ምክንያት ሲ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56554166 |
politics | መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ተገለጸ | የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ከህወሓት ጋር በሚደረገው የድርድር ሂደት እንደሚገፋበት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ። ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ. ም. ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቷ መንግሥት በዚህ ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ነው ይህንን ያሉት። “የአገሪቱን ጥቅም ባስከበረ” እንዲሁም “ዘለቄታን ባማከለ” መልኩ ከህወሓት ጋር የሚደረገውን ድርድር የፌደራል መንግሥቱ እንደሚቀ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn453yyr27eo |
health | ካናዳ ፋይዘር የተሰኘው ክትባት ለሕፃናት እንዲሰጥ ፈቀደች | ካናዳ ፋይዘር የተሰኘውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ከ12 እስከ 15 ዓመት ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጠች። ይህ ውሳኔ የኮሮናቫይረስ ክትባት በዚህ ዕድሜ ላሉ ህጻናት እንዲሰጥ የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል። የሶስተኛ ምዕራፍ ‘የክሊኒካል’ ሙከራ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ፋይዘር የተሰኘው ክትባትከ 12 እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናት እንዲከተቡ ይሁንታውን የሰጠው። “በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ላይ የተሞከረው ክትባቱ አስተማማኝና ውጤታማ ነው... | https://www.bbc.com/amharic/news-57029733 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኮቪድ ክትባት መስጠት ትጀምራለች ተባለ | የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም የአፍሪካ አገራት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ "ከፍተኛ ቅድሚያ" ለሚሰጣቸው ሰዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት መከተብ አለባቸው አለ። ኮቫክስ 90 ሚሊዮን ክትባቶችን ወደ አፍሪካ በቅርቡ ማሰራጨት ይጀምራል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የስርጭት መጠኑም የሚወሰነው አገራት ባላቸው የሕዝብ ብዛት መጠን መሆኑ ተመልክቷል። ለእያንዳንዱ አገር የሚከፋፈለው ክትባት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከፊት ተሰልፈው እየሰሩ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ብቻ የሚያገኙት ሳይሆን፣ ከፍተኛ ቅድሚያ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55950980 |
business | የአሜሪካ ሴኔት ቦይንግ አብራሪዎችን በተሳሳተ መልኩ አሰልጥኖ ነበር አለ | የአሜሪካ ሴኔት መርማሪዎች የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላኖችን የሚፈትሹ አብራሪዎችን 'ተገቢ ባልሆነ መልኩ' ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል ሲሉ ከሰሱ። በወራት ልዩነት ሁለት አደጋዎች ማጋጠማቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2019 ላይ እንዳያበሩ ታግደው ነበር። መርማሪዎቹ እንደሚሉት ቦይንግ እና የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) በመመሳጠር ስለአውሮፕላኖቹ ወሳኝ መረጃዎችን ሆን ብለው ለመደበቅ ሞክረዋል። ቦይንግ በበኩሉ በምርመራው የተገኙትን ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55375186 |
business | መርዛማ ሊድን አጋልጣ 423 ሚሊዮን ብር ያገኘችው ፊሊስ ኦሚዶ | ፊሊስ ኦሚዶ ኬንያዊት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 ላይ ለምትሠራበት ድርጅት ስጋቷን ስትገልጽ፤ ይህን ጉዳይ ዳግመኛ እንዳታነሺ ተብላ ነበር። ፊሊስ ትሠራበት የነበረው ድርጅት የሚያካሂደው የባትሪ መልሶ ጥቅም ላይ (ሪሳይክሊንግ) ሂደት የሰዎችን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል ነበር ለአሠሪዎቿ የተናገረችው። ነገር ግን ሰሚ ጆሮ አላገኘችም። በአሠሪዎቿ “ዝም በይ” ብትባልም ፊሊስ አልሰማቻቸውም። ያኔ 31 ዓመቷ ነበር። ገና ከዩኒቨርስቲ እንደተመረቀች ሞምባሳ የሚገኝ ‘ኬን... | https://www.bbc.com/amharic/news-53620643 |
politics | የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀመረ | የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ዛሬ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል፡፡ ከአረብ ሊግ የተወከሉ የምርጫው ታዛቢ ሁሉም ነገር በሰላም እየተካሄደ ነው ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከ 200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉሌህ ለ 22 አመታት አገሪቷን አስተዳድረዋል፡፡ የበቢሲው ዘጋቢ መሃመድ አብዲራሂም እንዳለው ዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫው የማስመሰል ምርጫ ነው በሚል ጥለው ወጥተዋል፡... | https://www.bbc.com/amharic/news-56686721 |
health | የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ | በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ "ማዕከል" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። "ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመ... | https://www.bbc.com/amharic/news-59165910 |
politics | በሶማሌ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላት መካከል የተከሰተው ምንድን ነው? | የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የቀድሞ አባላት ነን ያሉ አካላት የክልሉን ብልጽግና ፓርቲ 'ለማረም እና ለማስተካከል' በሚል እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ጅግጅጋ ላይ የተሰባሰቡ የፓርቲው የቀድሞ አመራሮች በቁጥር ከ10 በላይ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም ሌሎች የፓርቲው የቀድሞ አባላትና አመራሮች አብረዋቸው መኖራቸውን ገልፀዋል። ቡድኑ እንቅስቃሴውን 'የክልሉን ሕዝብ ለማዳን' በሚል መጀመሩን ጨምረው ተናግርዋል። የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60333655 |
politics | የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ኡጋንዳ በምርጫው ዋዜማ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ አደረገች | በዛሬው ዕለት ምርጫ በምታካሂደው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ከዋዜማው ጀምሮ እንዲቋረጥ መደረጉ ተገልጿል። የኢንተርኔትን ሁኔታ በበላይነት የሚቆጣጠር ኔት ብሎክስ የተሰኘው ቡድን በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ከትናንትና ምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ በመላው አገሪቱ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው። ይህ የባለስልጣናቱ ኢንተርኔት የማቋረጥ ውሳኔም በቅርቡ የትኛውም የትኛውም አይነት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ የተላለፈውንም ይከተላል። ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኑ እንዳሉት ፌስቡክ የፓርቲያቸውን ደጋፊዎች አ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55657685 |
health | በአሜሪካ የኮቪድ ክትባት ያልተከተበው ግለሰብ የልብ ንቅለ ተከላ ተሰረዘ | በአሜሪካ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ታካሚው የኮቪድ-19 ክትባት ባለመውሰዱ የልብ ንቅለ ተከላውን ሰረዘ። ዲጄ ፈርጉሰን የተሰኘው የ31 ዓመት ታካሚ አንገብጋቢ የሆነ የልብ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ቢሆንም በቦስተን የሚገኘው ሆስፒታል ግን ግለሰቡን ከታካሚዎች ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል። የብሪንግሃም እና የሴቶች ሆስፒታል የልብ ንቅለ ተከላውን የሰረዘው ታካሚው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ባለመውሰዱ ነው። የታካሚው ወላጅ አባት ዴቪክ፤ የኮቪድ ክትባት ከልጃቸው መሠረታዊ መርሆች ጋር የሚቃረን መሆኑን በመ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60136750 |
business | ኮሮናቫይረስ ፡ አርጀንቲና በኮቪድ-19 ሰበብ ባለሀብቶች ላይ አዲስ ግብር ጣለች | አርጀንቲና ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ሕክምና የሚያስፈልጉ የሕክምና አቅርቦቶችን ለማሟላትና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላትን ወጪ ለመሸፈን ሀብታም ዜጓቿ ላይ አዲስ ግብር ጣለች። ይህ አንድ ጊዜ የሚከፈለውና "የሚሊየነሮች ግብር" የተባለውን ታክስ ለመጣል የወጣው ረቂቅ ለአርጀንቲና ምክር ቤት አባላት ቀርቦ 26 እንደራሴዎች ቢቃወሙትም የ42ቱን ድጋፍ በማግኘቱ ጸድቋል። ይህ ግብር ይመለከታቸዋል የተባሉት የአርጀንቲና ባለጸጋዎች ሀብታቸው ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን ብዛታቸውም 12 ሺህ እንደሚሆኑ ታውቋል። ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55200359 |
politics | ተጨማሪ ሁለት ፓርቲዎች በሶማሌ ክልል ከሚደረገው ምርጫ እራሳቸውን አገለሉ | በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሶማሌ ክልል ተሳታፊ የነበሩ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አስታወቁ። በሶማሌ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት እጩዎችን አቅርበው የነበሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የነፃነትና የእኩልነት ፓርቲ (ነዕፓ) ከመጪው ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ከሁለቱ ፓርቲዎች በተጨማሪ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) መስከረም 20 ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል። ኦ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58640081 |
politics | የትግራይ ኃይሎች አላማጣና ኮረምን መቆጣጠራቸው ተነገረ | የትግራይ ኃይሎች በደቡባዊ ትግራይ የምትገኘውን ኮረም ከተማን መቆጣጠራቸው ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። ክልሉ ከጦርነቱ በፊት የነበረ ግዛቶችን በሙሉ ለማስመለስ እየተካሄደ ነው የተባለውም ጦርነት ወደ ደቡብ ክፍል መቀጠሉንም ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል። ሮይተርስ የህወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የትግራይ ኃይሎች ከመቀለ በስተደቡብ በኩል 170 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ኮረም ከተማ መቆጣጠራቸውን ነው። ሰኞ ዕለት አመሻሽ ላይ የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በደቡባዊ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57816164 |
business | ሮማን አብራሞቪች፡ ከማደጎ እስከ ቢሊየነርነት | ገና በሦስት ዓመቱ ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ዛሬ ላይ ከዓለማችን እጅግ ከናጠጡ ባለጸጎች መካከል ተጠቃሹ ነው፤ ሮማን አብራሞቪች። ሮማን አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያለው የጠበቀ ግንኙነት የገነባውን ገናና ስምና ንግድ እያሳጣው ይገኛል። ''እርግጠኛ ሰዎች ለሦስት ወይም አራት ቀናት እኔ ላይ ትኩረት ያደርጉ እና ከዛ ያልፋል። እኔ ላይ ትኩረት አያደርጉም። ማን እንደሆንኩኝ ቶሎ ይረሳሉ። እኔ ደግሞ ይሄ በጣም ነው የሚስማማኝ'' ብሎ ነበር ቢሊየነሩ የለንደኑን የእንግሊዝ ፕሪምየር... | https://www.bbc.com/amharic/news-60899537 |
business | ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ከስምምነት ደረሱ | ነዳጅ አምራች አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ እና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማቃለል ምርታቸውን ለማሳደግ ተስማሙ። በሁለት ዓመት ተኩል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ዋጋዎች ከጨመሩ በኋላ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) አባላት እና እንደ ሩሲያ ያሉ ከድርጅቱ ውጭ ያሉ አገራት ከነሐሴ ጀምሮ አቅርቦትን ያሳድጋሉ። እርምጃው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይም ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል። የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በዚህ ዓመት በ43 በመቶ ገደማ ጨምሮ በበርሜል ወደ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57884491 |
politics | ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ የተገደሉባት የቻድ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? | የሟቹ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ መጨረሻ አነሳሳቸውን የሚያስታውስ ነው። ዴቢ በ1990 (እአአ) በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነበር ስልጣን ከሄስኔ ሃበሬ የቀሙት። በተመሳሳይም ፕሬዝዳንት ዴቢ ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚፈልጉት አማጽያን ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸው አለፈ። ከስልጣን ሊያወርዷቸው በሚታገሉት አማጽያን እጅ ሞትን ተቀበሉ። ዴቢ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላም ጦር ሜዳ እየተገኙ ወታደሮቻቸውን ይጎበኛሉ። "ተዋጊው መሪ" በመባል የሚታወቁት ዴቢ ነሐሴ 2020 ከገዢው ከፓትሪዮቲክ ሳልቬሽን ሙቭመንት... | https://www.bbc.com/amharic/56828901 |
sports | ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፍ እድላቸው ምን ያህል ነው? | በካሜሮን እዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ያደርጋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈትን ያስተናገዱት ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋቸውን ከቡርኪና ፋሶ ጋር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ። ዋልያዎቹ በመጀመሪያው ጨዋታቸው በኬፕ ቬርድ 1 ለ 0፤ በሁለተኛው ግጥሚያ ደግሞ በአዘጋጇ ካሜሩን 4 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል። ለመሆኑ ዋልያዎቹ ከምድባቸው የማለፈ እድላቸውም ምን ያህል ነው? መልሱ - ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60020563 |
business | ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? | የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከጅማሮው በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ አንድ ዓመት አስቆጠሩ። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው በድንገት አልፎ ከተገኘ በኋላ፤ በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራው እንደደረሰበት ማሳወቁ ይታወሳል። መኪናቸው ውስጥ የተገኘውም ሽጉጥ የኢንጂነሩ እንደነበር በምርመራው አረጋግጫለሁ ብሏል። •ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍ... | https://www.bbc.com/amharic/news-49027549 |
business | ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው | ህንድ ከእሁድ ጀምሮ የለውዝና የአፕል ምርቶችን ጨምሮ 28 የአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ ልታስተዋውቅ መሆኑን ገልፃለች። አዲሱ ታሪፍ ህንድ የብረትና አሉሚኒየም ምርቶችን ወደ አሜሪካ በምትልክበት ወቅት ለጫነችባት ከፍተኛ ግብር ምላሽ ነው ተብሏል። አሜሪካ ግብሩን ዝቅ አድርጊ ብትባል በእምቢተኝነቷ ቀጥላለች። በዚህ ወር ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለህንድ በንግዱ ዘርፍ የምታደርግላትን የተለየ ጥቅማጥቅም እንደምታቆም ገልፀው ነበር። •ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ •ኢኮ... | https://www.bbc.com/amharic/news-48652222 |
politics | የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ በወታደራዊው ኃይል ተቃውሞ ሦስት ሰዎች ተገደሉ | በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍና ወታደራዊ ኃይሉን በመቃወም አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተኮሱት ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሐኪሞች ኮሚቴ አስታወቀ። ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣን እንዲመለሱ በዋና መዲናዋ ካርቱም እና በሌሎች ከተሞች አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል። የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ በተቃዋሚዎች ላይ ተኩሰዋል መባሉን ሀሰት ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት... | https://www.bbc.com/amharic/news-59066441 |
politics | በአገር ውስጥ ጉዳይ የተወጠሩት ባይደን ስብሰባ ለመሳተፍ አውሮፓ ገቡ | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 2.75 ትሪሊየን ዶላር የሃገር ውስጥ አጀንዳቸውን በዋሽንግተን በመተው ለሁለት ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች አውሮፓ ገብተዋል። ባይደን በዩናይትድ ኪንግደም የአየር ንብረት ኮንፈረንስ ላይ ለሌሎች የዓለም መሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ዕቅዳቸውን ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። የተሰሚነት ደረጃቸው እየቀነሰ የመጣው ባይደን፤ የስልጣን ዘመናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ፕሬዚዳንቱ ራሳቸው ተናግረዋል ። ባይደን ለጂ20 ስብሰባ ዓርብ ጠዋት ሮም ደርሰዋል። በስብሰባው የዓለም ዝቅተኛ የግብር ... | https://www.bbc.com/amharic/59074461 |
business | በዓመት 2ሚሊዮን ብር የሚያስከፍለው ትምህርት ቤት ጥቁሮችን ይቅርታ ጠየቀ | የኢትን ትምህርት ቤት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኝና በትምህርት ጥራቱ የገነነ ሥመ ጥር እንዲሁም ውድ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት የአሁኑን ጠቅላይ ሚኒትር ቦሪስ ጆንሰንን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦችና ሌሎች ሥመ ጥር ፖለቲከኞች ተምረውበታል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ታዲያ ለመጀመርያው የትምህርት ቤቱ ጥቁር ተማሪ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ደራሲ ዲሊቤ ኦኒያማ ከኢትን ኮሌጅ ለመመረቅ የመጀመርያው ጥቁር ነው፡፡ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ማትሪክ) የወሰደው እንደ አውሮፓዊያኑ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53148768 |
sports | ደራርቱ ቱሉ፡ ከ30 ዓመት በፊት ለአፍሪካ ሴቶች የተተከለ የድል ችቦ | ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ነግሳ ከቆየች ድፍን 30 ዓመታት ተቆጠሩ። ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ገብታ መኖር የጀመረችው የባርሴሎና ኦሊምፒክን ተከትሎ ነው። በባርሴሎና ደግሞ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም ፈር የቀደደ ድል ነበር ያስመዘገበችው። ሳቂታዋ ደራርቱ በሩጫው ሜዳ ብቻ ሳይሆን በስፖርት አስተዳደርም ስሟ በበጎ ይነሳል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት፣ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ በምክት ፕሬዝዳንትነት እና በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ደግሞ ኢትዮጵ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c891j8lrn81o |
politics | ባይደን እና ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ 'ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ' ፍለጋ ሊወያዩ ነው | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ ሊወያዩ ነው። መሪዎቹ ሐሙስ ዕለት በስልክ ይነጋገራሉ ተብሏል። እንደዋይት ሐውስ ባለሥልጣን ከሆነ ፕሬዝዳንቶቹ በአገሮቹ መካከል በቀጣይ ስለሚደረጉ የፀጥታ ውይይቶች እና በአውሮፓ ባለው ሁኔታ ላይ ይወያያሉ። ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ጦር ያሰፈረችው ሩሲያ አገሪቱን ለመውረር አላቀድኩም ስትል አስተባብላለች። ሩሲያ ወታደሮቿ በቦታው ለልምምድ መገኘታቸውን ጠቅሳ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-59825257 |
business | በሩሲያዊው አሌክሴ መታሰር ምክንያት የ11 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ሊቋረጥ ይችላል ተባለ | ሩሲያና አውሮፓን የሚያስተሳስረው ንግድ በዋዛ የሚታይ አይደለም። አውሮፓ 40 ከመቶ ጋዝ የምታገኘው ከሩሲያ ነው። አሁን ደግሞ እጅግ ግዙፉ የጋዝ ማስተላለፍያ ቧንቧ ከሩሲያዋ ኪንጊሴፐን እስከ ግራስዋልድ ጀርመን ድረስ የሚዘረጋ ነው። ይህ ፕሮጀክት በርካታ አገራትን የሚያቋርጥና በባልቲክ ባህር ስምጥ ተቀብሮ የሚያልፍ ውስብስብ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ጀርመንን የሩሲያ የኢኮኖሚ እስረኛ ሊያደርጋት ይችላል የሚለው ስጋት ገና ከፕሮጀክቱ መጠንሰስ ጀምሮ ሲነገር የነበረ ነው። አሁን ደግሞ ጀርመንና ሩሲያ በአ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55761773 |
politics | በሊባኖስ ጉዳት ባደረሰው ፍንዳታ የተቆጡ ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ጥቃት ፈጸሙ | ሊባኖስ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፈንድቶ ሞትና ጉዳት ካደረሰ በኋላ ተቃዋሚዎች በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤት ላይ ጥቃት ፈጸሙ። እሁድ ዕለት በደረሰው ነዳጅ ፍንዳታ 27 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 79 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ይህንን ተከትሎም በርካታ ተቃዋሚዎች ናጂብ ሚካቲ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤትም ላይ ድንጋይ በመወርወር ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። ሚካቲ የተቃዋሚዎቹን ሐዘን እንደተረዱ የገለጹ ሲሆን "ተቀባይነት የሌለው ጥፋት" ያሉትን የተቃዋሚዎቹን ድርጊት አውግዘዋል። የአገ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58223897 |
business | ሮበርት ሙጋቤ በባንካቸው ውስጥ ያልተናዘዙት አስር ሚሊዮን ዶላር ተገኘ | የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስር ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችም በመዲናዋ ሐራሬ ትተው ማለፋቸውን የሃገሪቱ የመንግሥት ጋዜጣ 'ሔራልድ' ዘግቧል። ባለፈው ዓመት መስከረም በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት ሙጋቤ ለገንዘቡም ሆነ ለቀሪው ንብረታቸው ወራሽ ማን እንደሆነ ኑዛዜ ባለማስቀመጣቸው የመንግሥት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ሆኗል። ይህንን ጉዳይ ለመወሰን ስብሰባ ተቀምጠው ነበር። •ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት "በካንሰር" ነው ተባለ •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት የቀድሞው ... | https://www.bbc.com/amharic/news-50640487 |
politics | ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ ደካማ ነው አሉ | የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ወጪ ንግድ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ “ደካማ” ነው ሲሉ ተቹ። አርብ ዕለት የጸደቀው የዋጋ ገደብ የሩሲያን ድፍድፍ ነዳጅ የሚገዙ አገራት በበርሜል ከ60 ዶላር በላይ እንዳይከፍሉ ለማድረግ ያለመ ነው። ሩሲያ በነዳጅ ምርቶች ወጪ ንግድ ላይ የተጣለውን የዋጋ ገደብ እንደማትቀበል አሳውቃለች። በመጪው ሰኞ ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ጣሪያ ምዕራባውያን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ ጋር ተያይዞ እያደረጉት ያለው ጫና አካል ነው። ነገር ግ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c1ve0drlrzvo |
business | የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው ተባለ | ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የፋይናንስ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያቅማሙ ነው። ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የመክፈል አቅሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ነው። በገንዘብ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ለምሳሌ የቻይናው ኤክዚም ባንክ እሰጣለው ብሎ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናው... | https://www.bbc.com/amharic/news-58246656 |
politics | እስራኤል-ጋዛ፡ ኔታንያሁ የሃማስ ታጣቂዎች ለዓመታት ወደ ኋላ ተመልሰዋል አሉ | እስራኤል በጋዛ ያደረገችው የዘጠኝ ቀናት ድብደባ የሃማስ ታጣቂዎችን በበርካታ ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ተናገሩ። የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ጋብ አላለም። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ወደ ደቡባዊ እስራኤል በተኮሱት ሮኬት ሁለት የውጭ አገር የእርሻ ሠራተኞች ተገድለዋል። እስራኤልም በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ ቀጥላለች። በዌስት ባንክ በራማላህ አቅራቢያ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ ሦስት ፍልስጥኤማዊያን በእስራኤል ፖ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57167680 |
politics | አንዳንድ ነጥቦች አዲስ ስለሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን | ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ይህንን ሂደት የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችና ልሂቃን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችና ሐሳቦችን መሠረት በማድረግ እንዲቀራረቡ በማድረግ ለአገራዊ አንድነት ገንቢ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አገራዊ ምክክሩ አውንታዊ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የሚቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለአስር... | https://www.bbc.com/amharic/news-59822579 |
business | በህንድ በመጠጥ መመረዝ የበርካቶች ህይወት አለፈ | በህንድ በመጠጥ መመረዝ የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ግለሰቦቹ በህገወጥ መንገድ የተመረተ አልኮል በመጠጣታቸው ህይወታቸው ማለፉን የሰሜን ህንዷ ግዛት ፑንጃብ ኃላፊዎች አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለት ፖሊስ አካባቢውን በመቆጣጠር ህገወጥ የተባለውን መጠጥ የያዘ ሲሆን መጠጡን ያመርታሉ የተባሉ 25 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የሟቾችም ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው ተብሏል። በህንድ በመጠጥ መመረዝ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሲሞቱ አዲስ አይደለም፤ በተደጋጋሚም የሚከሰት ችግ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53627129 |
health | ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ | በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣... | https://www.bbc.com/amharic/57111329 |
sports | ለንደን ማራቶን፡ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከኬንያዊው ኪፕቾጌ የማራቶን ድል እንዲነጥቅ የረዳው ምንድን ነው? | ኤሉድ ኪፕቾጌን ለማሸነፍ እንዴት ያለ ወኔ ይበቃ ይሆን? ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠውን ብርቱ አትሌት ለማሸነፍ ምን ሲደረግ ይቻላል? ጥብቅ ልምምድ ወይስ ተሰጥኦ? ለለንደን ማራቶን አሸናፊው ሹራ ቂጣታ ግን ጥሩ ቁርስ በቂ ነው። ባለፈው ዓመት በዩኬ ዋና ከተማ አራተኛ በመሆን ነው ያጠናቀቀው። ያኔ ኬኒያዊው ኪፕቾጌ ነው ያሸነፈው። በወቅቱ ሹራ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ባዶ ሆዱን መሮጡን፣ ለቁርስ ፍራፍሬ ብቻ መመገቡን ገልጾ ነበር። ሹራ በወቅቱ 35 ኪሎ ሜትሮች ከሮጠ በኋላ የተሰማውን ሲያሰፍር "ሆ... | https://www.bbc.com/amharic/54546131 |
business | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ? | በመላው ሃገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎችና በትልቅነቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት አስተካክሎ መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የአብሥራ ከበደ ለቢቢሲ ገለፁ። • በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ • የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ? ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተለመደውን ... | https://www.bbc.com/amharic/news-49260745 |
politics | የአውሮፓ ሕብረት የአውሮፕላን እስርን ተከትሎ በቤላሩስ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ | የአውሮፓ ሕብረት የቤላሩስ አየር መንገድ በአውሮፓ ሰማይ ላይ እንዳይበር ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ሕብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው እሁድ ዕለት በበረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን አንድ ጋዜጠኛን ለመያዝ ሲል አቅጣጫውን እንዲለውጥ ተገዶ ሚንስክ እንዲያርፍ መደረጉን ተከትሎ ነው። በብራስልስ በተካሄደው ስብሰባ የ27ቱ አባል አገራት መሪዎች የአውሮፓ ሕብረት አየር መንገዶችም በቤላሩስ ሰማይ ላይ ድርሽ እንዳይሉ ተናግረዋል። ሕብረቱ ሌሎች ተጨማሪ ምጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦችን እንደሚጥልም አስታውቋል... | https://www.bbc.com/amharic/news-57230080 |
health | ኢትዮጵያ፡ ‘የማይናገሩት’ እና ‘የማይነገርለት’ የተንሰራፋው የወጣቶች ጭንቀት | በብዙ ምክንያቶች ማንነቷ እንዲታወቅ አትፈልግም። እኛም እንዳትታወቅ በሚል ‘ቅድስት’ በሚል ስም እንጠራታለን። ቅድስት ዘንድሮ ነው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዋን የወሰደችው። ከቢቢሲ ጋር ዛሬ ያገናኛት ጉዳይ ግን የተከሰተው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ገና አስረኛ ክፍል እያለች። “አንድ እኛ ትምህርት ቤት ከሚማር ልጅ ጋር የዐይን ፍቅር ይዞኝ ነበር” ስትል ትጀምራለች። አፍላ ፍቅር። በጓደኞቿ ግፊት ፈራ ተባ እያለች ‘የልቤን’ ያለችውን ነገረችው። ምላሹ ግን የልቧን አላደረሰውም። አዘነች። ተከፋች። ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c5152vjxv3no |
health | ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች | የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56330257 |
politics | እነ አቶ ጀዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍቃድ ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ | አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፍ ለሁለተኛ ጊዜ በራሳቸው ፍላጎት ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የዛሬውን ቀጠሮ ይዞ የነበረው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በሚሰሙበት ሁኔታ ላይ ክርክር ለማድመጥ እና ከዚህ ቀደም ችሎት ሳይገኙ የቀሩት ተከሳሾች ከችሎት የቀሩበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ነበር። በዛሬው ችሎት በእነ አቶ ጀዋር የክስ መዝገብ ስር ከተዘረዘሩ ተከሳሾች መካከል ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት አራት ግለሰቦችን ጨምሮ አቶ አማን... | https://www.bbc.com/amharic/news-57737839 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ ዶ/ር ፋውቺ ለክትባት መጣደፉ ቢቀርብን ይሻላል አሉ | የአሜሪካ ዕውቅ የማኅበረሰብ ጤናና የተላላፊ በሽታዎች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ‹‹እኔ ተናግሪያለሁ! ይሄ ለክትባት የምንጣደፈው ነገር አላማረኝም›› እያሉ ነው፡፡ ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የመጪው ምርጫ በለስ እንዲቀናቸው በሙከራ ላይ ያለን ክትባት ያለጊዜው ወደ ሕዝብ በማውጣት ‹ክትባት ደርሷልና ተከተቡ› እንዳይሉ ስጋት መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡ ዶ/ር ፋውቺ በአሜሪካ ህዝብ ከትራምፕ የበለጠ ተሰሚነትና የመታመን ፀጋን ያገኙ ጎምቱ የጤና ባለሞያ ናቸው፡፡ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53900469 |
politics | የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው ድርድር የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ | የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማብቃት እንዲቻል የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥትን እና የትግራይ ኃይሎችን ድርድር እንዲጀምሩ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ነበር ጥሪ ያቀረበው። መንግሥት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አረጋግጧል። የአፍ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgrd55vr82go |
sports | ኢትዮጵያ ጫፍ በደረሰችበት የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሰባት አገራት ትላንት ተለዩ | ትላንት በተካሄደ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ተጨማሪ ሰባት አገራት ተለዩ። ጋምቢያ፣ ኮሞሮስ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ዚምባብዌ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ናቸው ወደ አህጉራዊው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት አገራት ናቸው። ጋምቢያ አንጎላን በሜዳዋ 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አልፋለች። በምድብ አራት የምትገኘው ጋምቢያ ከሁለቱ አላፊ ቡድኖች አንዷ የሚያደርጋትን ወሳኝ ጎል አሳን ሴሳይ ከዕረፍት መልስ አስገኝቷል። በዚህ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56539796 |
business | ኤሎን መስክ ለትዊተር ሰማያዊ ምልክት በወር ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ | ኤሎን መስክ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት (ገጽ) መሆኑን የሚያመለክተውን ሰማያዊ ምልክት በስማቸው ለሚፈልጉ የትዊተር ተጠቃሚዎች ወርሃዊ ስምንት ዶላር እንደሚያስከፍል ተናገረ። በ44 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ የማህበራዊ ድረ-ገጹን ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ይህንን የወሰነው “የማያስፈልጉ መረጃዎችንና ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር ነው” ብሏል። በትዊተር አካውንት ከተጠቃሚዎች ስም ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ ምልክት በዋነኝነት ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ገጻቸውን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙበት ሲሆን ክፍያም የለውም። ይህ እርምጃ አ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c72z7eg9600o |
sports | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ... | https://www.bbc.com/amharic/53864758 |
politics | የትራምፕ መኖርያ ቤት በፖሊስ መፈተሹን ተከትሎ የፀጥታ አካላት እንዳይገደሉ ተፈርቷል | ባለፈው ሳምንት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት (ማር ኤ ላጎ) ላይ ድንገተኛ አሰሳና ፍተሻ ተደርጎበት ነበር። ይህን ተከትሎ በአሜሪካ የፀጥታ አካላት ላይ ስጋት ነግሷል። በድርጊቱ የተቆጡ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይል አባላትን እያስፈራሩ ነው። የአሜሪካ የፀጥታ እና ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለባልደረቦቻቸው ባስተላለፉት የተጠንቀቁ መልዕክት ‘አደጋ እንደተደቀነባችሁ አውቃችሁ በጥንቃቄ ተንቀሳቀሱ’ ሲል ያሳስባል። ከዚህ የትራምፕ መኖሪ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c03z223d85no |
politics | ኡሁሩ ኬንያታ በአገራቸውና በአካባቢው አገራት እንዴት ይታወሳሉ? | ከኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ በሚነሱ የሰላም ድርድሮች ላይ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በበለጠ ሲጠቀሱ ይሰማል። በተለይም የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ወገንተኝነትን አሳይተዋል በሚል በትግራይ ኃይሎች የሚወቀሱ ሲሆን፣ በትግራይ ያለውን ሁኔታ እንደተከታተሉት የተነገራላቸው ኡሁሩም አደራዳሪ ይሁኑ ሲሉም ተሰምተዋል። ከአምስት ወራት የተኩስ አቁም አዋጅ በኋላ ያገረሸው ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ የተለያዩ ተቋማትና አ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/crg2q0dv1gvo |
business | አልጄሪያ ለሥራ አጦች ወርሃዊ ክፍያ ልትሰጥ ነው | ከፍተኛ የሥራ እጦት ባለባት አልጄሪያ መንግስት ለወጣቶች የሥራ አጥነት ድጎማ እንደሚጀምር ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ። ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ተቡን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከ19 እስከ 40 ዓመት ለሆናቸው ሥራ ፈላጊዎች ከመጋቢት ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያ ያገኛሉ። ለክፍያው ብቁ የሆኑ ዜጎች ሥራ እስኪያገኙ ድረስ በወር ወደ 100 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እና አንዳንድ የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ። ተቡን አክለውም ይህን መሰሉን ጥቅማ ጥቅም በማስተዋወቅ ከአውሮፓ ውጪ አልጄሪያ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን አስታውቀዋል።... | https://www.bbc.com/amharic/news-60387663 |
health | የካንሰር ህዋስን የሚገድለው ቫይረስ ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ እንደሚሰጥ ተገለጸ | ቫይረስ በመጠቀም የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተገለጸ። የዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ በዚህ ሕክምና አንድ ካንሰር ታማሚ ሲፈወስ ሌላ ታማሚ ደግሞ ከፍተኛ ማገገም አሳይቷል። ለሕክምና የዋለው ቫይረስ በዋናነት የጉሮሮ መከርከር የሚያስከትለው ኸርፕስ ሲምፕሊክስ ሲሆን፣ ቫይረሱ እንዲዳከም ተደርጎ ነው ጥቅም ላይ የዋለው። በሕክምናው ዙሪያ ተጨማሪ ጥናቶች ቢያስፈልጉም፣ ለካንሰር ሕሙማን ተጨማሪ ዕድሜ የመስጠት ተስፋ እንዳለው ሳይንቲስቶች ገልጸዋል... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c19jrd08nl2o |
sports | የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020፡ የትኞቹ አገራት የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 የሜዳሊያ ሰንጠረዥ | የ2020ው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ከዚህ በፊት ከተካሄዱት በበለጠ በ33 የስፖርት አይነቶች ውድድሮች የሚካሄድበት ነው። ባለፈው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ይህ የኦሊምፒክ ውድድር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደዚህኛው ዓመት የተሸጋገረ ሲሆን ውድድሩ ጃፓን ውስጥ በሚገኙ 42 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ይካሄዳል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚደረጉ ውድድሮች አገራት የሚያገኙትን የሜዳሊያ ዝርዝሮች የያዘ ሰንጠረዥ ነው። በዚህ ሰንጠረዥ ላይ ተወዳዳሪዎች የሚያገኙት ሜዳሊያ ከሚወክሉት አገ... | https://www.bbc.com/amharic/57662275 |
politics | ባይደንን ከሞት ያተረፏቸው አፍጋናዊ አስተርጓሚ አሜሪካ ገቡ | ጆ ባይደን ሴናተር እያሉ አፍጋኒስታን ውስጥ ከአደጋ ያተረፏቸው አስተርጓሚና ቤተሰቦቻቸው ጓዛቸውን ጠቅልለው ከሃገራቸው መውጣታቸው ተሰምቷል። ጊዜው 2008 ነበር። በፈረንጆቹ። የአሁኑ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና ሌሎች ሴናተሮችን የያዘ ሄሊኮፕተር በከባድ አየር ምክንያት ከአንዲት የአፍጋኒስታን መንደር ለማረፍ ይገደዳል። ሥፍራው ለወትሮው የበረዶ ጥጥ የሚዘንብበትና ታጣቂዎች ጥቃት አከታትለው የሚያደርሱበት ነው። አማን ካሊል በአሜሪካ መንግሥት ተቀጥረው ከሚሠሩ አፍጋናዊያን መካከል ነበሩ። አሜሪካዊያኑን ሴናተ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58880580 |
sports | አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ | የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትናንትናው እና በዛሬው እለት ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ኢሳያስ ጅራ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ። ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸንን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት እንደተመረጡ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ሶስት እጩዎች ቀርበው የነበረ ሲሆን በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ እንዲሁም አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ አግኝተዋል። ሦስቱ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1q65nw626o |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.